ከማንበቢያ ዝርዝር ንጥል ነገሮችን ወደ Microsoft Edge አንቀሳቅስ
በ Windows 10 ውስጥ አዲስ አሳሽ በሆነው በ Microsoft Edge ውስጥ ውስጠ ግንቡ የንባብ ዝርዝር ይገኛል። በ Windows 8.1 ውስጥ ያለውን የንባብ ዝርዝር መተግበሪያ ከተጠቀሙ እና አሁን ወደ Windows 10 ደረጃ ከፍ ካደረጉ፣ ከአሮጌው መተግበሪያ ላይ ያሉትን ንጥሎች ወደ Microsoft Edge ያንቀሳቅሱ።
በ Microsoft Edge ለመክፈት፤ በንባብ ዝርዝር መተግበሪያው ላይ አንድን ንጥል ይምረጡ። (ሌላ ማሰሻ ላይ ከተከፈተ፤ በመጀመሪያ ወደ ጅማሬ ይሂዱ፤ ከዛ የክንውን አውዶች > ስርዓት > ነባሪ መተግበሪያዎች በመቀጠል የእርስዎን ነባሪ የድር አሳሾች ወደ Microsoft Edge ይለውጡ።)
በ Microsoft Edge ውስጥ፣ የኮከብ አዶውን ይምረጡ፣ ይምረጡ የንባብ ዝርዝር፣ እና በመቀጠል ይህን ይምረጡ ያክሉ።